Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የተለያዩ የክልሉ አመራሮች ልኡክ ጅግጅጋ የገባ ሲሆን ፥ ልኡካን ቡድኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና የተለያዩ የክልሉ የመንግስት የስራ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳና ልኡካቸው ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ጋር በመወያየት በክልሉ ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ የሚሆን የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.