Fana: At a Speed of Life!

የወሎ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎቹን ከየካቲት 30 ጀምሮ ሊቀበል ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎቹን ከየካቲት 30 ጀምሮ ሊቀበል መሆኑን አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ብርሀኑ አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ዩኒቨርሲቲው በሸብር ቡድኑ ከፍተኛ ውድመት ቢደርስበትም በመልሶ ግንባታ የመማር ማሰተማር ስራን መከወን የሚችልበት አቋም ላይ ይገኛል ብለዋል።

ተቋሙ ከአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ድጋፍ ማግኘቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ ፥ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ከየካቲት 30 ጀምሮ ጥሪ ያደርጋል ብለዋል።

ቀሪ መደበኛ ተማሪዎች በቀጣይ ጊዜ እንደሚጠሩ የተገለጸ ሲሆን ፥ የርቀት ትምህርት ተማሪዎች ከየካቲት 12 ጀምሮ የቲቶሪያል ትምህርት እንደሚሰጣቸው ዶክተር ብርሀኑ ገልጸዋል።

በከድር መሀመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.