ከተማ አስተዳደሩ በባሌ ዞኖች በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ከ78 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በባሌ እና ምሥራቅ ባሌ ዞኖች በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ከ78 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አድርጓል፡፡
ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን ለመርዳት የከተማው አስተዳደር ከባለሃብቶችና ከከተማው ማህበረሰብ ያሰባሰበውን ከ78 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዕለት ደራሽ ድጋፍ ዛሬ በሮቤ ከተማ አስረክቧል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፥ በመካከላችሁ የተገኘነው በተግባር ችግራችሁን በመካፈል አብረናችሁ እንዳለን ልናሳይ ነው ብለዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች ከ78 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት እርዳታ ከህዝብ መሰብሰቡን ጠቁመው፥ ከጎደለው ያካፈለንን የአዲስ አበባ ነዋሪ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ወደፊትም የከተማ አስተዳደሩ እና የአዲስ አበባ ሕዝብ በማንኛውም ጊዜ ከባሌ ህዝብ ጎን እንደሚቆምም ማረጋገጣቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱላኪም አሊዪ እና የምስራቅ ባሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቱ በቀለ በበኩላቸው፥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!