Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሶማሌ ክልል በተከሰተ ድርቅ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና ልዑካቸው ድጋፉን ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ አስረክበዋል።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፥ የሶማሌ ክልል ባለው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ እና የመልማት አቅም ለቀጣይ የኢትዮጵያ ብልፅግና ዋልታና መሰረት መሆን የሚችል ክልል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመቀነስ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረትም አድንቀዋል።

በዚህም የሲዳማ ክልል የክልሉን መንግስት እና ማህበረሰብ ለመደገፍ የሚያስችል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በተደረገው ድጋፍ በሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ሙስጠፌ የሲዳማ ክልል አደረጃጀት በሂደት ላይ ባለበት ወቅት ይህንን ድጋፍ ማድረጉ የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን የሚያጎለብት መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሎች መካከል እየታየ ያለው መደጋገፍ እና ትስስርም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አቶ ሙስጠፌ መግለጻቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.