Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አምስት የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ተጨማሪ አምስት የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ከፈተ፡፡
 
ድርጅቱ ከአዲስ አበባ እስከ ጅቡቲ በሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ ቀደም 14 ጣቢያዎች የነበሩት ሲሆን÷ ተጨማሪ አምስት ጣቢያዎችን በመክፈት የጣቢያዎቹን ቁጥር ወደ 19 ከፍ ማድረግ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡
 
ጣቢያዎቹን መጨመር ያስፈለገው የአገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት መሆኑን ኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ሳርካ ተናግረዋል፡፡
 
ተጨማሪ ጣቢያዎቹ ከአዲስ አበባ እስከ ድሬዳዋ ባሉ አካባቢዎች በሚገኙ ወረዳዎችና ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርም ነው ያነሱት፡፡
 
ተጨማሪ ጣብያዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ድርጅቱ ተጨማሪ ጣቢያዎቹን ስራ ባስጀመረበት መርሃ ግብር ላይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቻዎ ቺዩዋን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.