Fana: At a Speed of Life!

የዳጉሩ -ጋላሞ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ- ጅቡቲ የጋላፊ ኮሪደር አካል የሆነው የዳጉሩ -ጋላሞ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

በጅቡቲ ሳዑዲ አረቢያ መንግስታት መካከል በተደረሰው የትብብር ሥምምነት መሠረት የሳዑዲ የልማት ፈንድ ለመንገድ ግንባታው በሰጠው የፋይናንስ ድጋፍ የግንባታ ሥራው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጅቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል ሀመድ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ሀሰን ሁሙድ ኢብራሂም፣ በጅቡቲ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር፣ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የጅቡቲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የመንገድ ግንባታው የኢትዮ- ጅቡቲ ኮሪደር አካል መሆኑና የሁለቱን ሀገራት ትሥሥር ከማጠናከርና የኢትዮጵያን የወጪ ገቢ ምርቶች ከማሳለጥ አኳያ የሚኖረው አስተዋፅዖ ከፍተኛ እንደሆነ መነሳቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከጅቡቲ ወደቦች ወደ ኢትዮጵያ የሚጓጓዙ ምርቶችን በተቀላጠፈ መንገድ ለማጓጓዝ የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ በመኪኖች ላይ ይደርስ የነበር ጉዳት እና የጊዜ መጓተትን በእጅጉ ይቀንሳልም ተብሏል፡፡

ግንባታውን የቻይናው ኩባንያ ‘‘CCECC’’ የሚያከናውነው ሲሆን ፥ የጅቡቲ-ዲኪል-ጋላፊ ኮሪደር አካል ነው፡፡

በኮሪደሩ የ20 ኪሎ ሜትር መንገድ ከኢትዮጵያ ድንበር አንስቶ እስከ ጋላፊ በጃፓኑ ኩባንያ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ፥ ቀሪው የጋለሞ – ሞሉድ 35 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ድርጅት እንዲገነባ ስምምነት ላይ ተደርሶ ቅድመ ዝግጅቶች በመካሄድ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.