Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሠር ካሣሁን ብርሃኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምሕርት ክፍል መምሕርና ተመራማሪ የነበሩት ፕሮፌሠር ካሣሁን ብርሃኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ፕሮፌሠር ካሣሁን ላለፉት 36 ዓመታት በዩኒቨርስቲው በመምህርነትና ተመራማሪነት እንዲሁም በልዩ ልዩ ከፍተኛ የኃላፊት ዕርከኖች ከማገልገላቸው በተጨማሪ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማበርከት ይታወቁ ነበር፡፡

የፕሮፌሠር ካሣሁን የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሠዓት በየካ ሚካኤል ቤተ ክስርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.