በወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተችሏል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማዳን መቻሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ፌደሬሽን ገለጸ፡፡
የፌደሬሽኑ የ2014 ዓም የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት ወጣት ሱልጣን አሊ÷ የክልሉ ወጣቶች ፌደሬሽን ዋነኛ አላማ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እውን ማድረግ ነው ብሏል።
በክልሉ በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን÷ ከ7 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተጠቁሟል።
በዚህም መንግስት ሊያወጣው የነበረውን 1ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉን ነው ፕሬዚዳንቱ ያስረዳው።
ፌደሬሽኑ ባለፉት 6 ወራት ትኩረት ሰጥቶ በሰራቸው ተግባራት ለውጥ ማምጣት መቻሉን የገለጸው ወጣት ሱልጣን÷ ‘እኔም የዘማች ቤተሰብ አካል ነኝ’ በሚል መሪ ቃልም 15 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን አስረድቷል።
በዚህም ከ5 ሺህ በላይ የዘማች ቤተሰቦችን መደገፍ ተችሏል የተባለ ሲሆን÷ መቶ ለወገኔ በሚል መርህ 1ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በማሰባሰብ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ መደረጉንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!