Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ግንኙነት አጠናክረን መቀጠል እንፈልጋለን- የሩስያ ፌዴሬሽን ሴናተር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር በሩስያ ፌዴሬሽን ሴናተር አይጎር ሞሮዞቪ የተመራ የልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
ኢትዮጵያና የሩስያ ፌዴሬሽን ከ123 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን÷ ሀገራቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ግንኙነታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ተመላክቷል፡፡
ላለፉት በርካታ ዘመናት የሩስያ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ በተለይም በትምህርት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች፣ በአቅም ግምባታ እያደረገች ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን አፈ ጉባዔ አገኘሁ አንስተውላቸዋል።
ሩስያ በፀጥታዉ ምክር ቤትም ሆነ በሌሎች መድረኮች ከጎናችን በመቆም ያሳየችውን እዉነተኛ ወዳጅነት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ምንጊዜም እንደማይረሱት ለሴናተሩ ጨምረው አብራርተዋል፡፡ ይኸው አጋርነትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን የገለፁት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር÷ ለሠላማዊና ልማታዊ ዓላማ የሚውል ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እያገባደደች መሆኑን ገልጸውላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ማንንም የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላትም አፅንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።
ሴናተር አይጎር ሞሮዞቪ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያና ሩስያ ግንኙነት ታሪካዊ መሆኑን ገልፀው ከኢትዮጽያ ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት አጠናክረው መቀጠል እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። በሩስያ ና ዩክሬን መካከል የተፈጠረውን ችግር ለአፈጉባዔ አገኘሁ አስረድተዋል፡፡
አቶ አገኘሁ ተሻገርም በሩስያ ና ዩክሬን መካከል የተፈጠረው ግጭት በውይይትና በሠላማዊ መንገድ እንደሚፈታ ያላቸውን እምነት ለሴናተሩ መግለጻቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.