Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ከ955 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ955 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ መሐመድ ሀሰን ÷በበጀት ዓመቱ በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ ሰፊ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ነው ያመለከቱት።

በዚህም በመጀመሪያው ግማሽ የበጀት ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ከ955 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ክንውኑ የዕቅዱን 80 በመቶ ቢሆንም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው ገልጸው፤ ግብሩ የተሰበሰበው ቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆነ እንዲሁም ታክስ ካልሆነ ግብር ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.