በሐረሪ ክልል በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ማጠናከር ይገባል – ዶ/ር ሊያ ታደሰ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ማጠናከር እንደሚገባ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ከሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ጋር በመሆን በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማስተባበሪያ ማእከልና የአውበርከሌ ጤና ኬላን ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ወቅትም ሚኒስትሯ እንዳሉት፥ በማእከሉ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ፈጣን ምላሾችን ለመስጠት እየተደረጉ የሚገኙ ጥረቶችን ተመልክተናል።
በተለይም ህብረተሰቡን ከአደጋ ከመጠበቅ አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራት የበለጠ እንዲጠናከር ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጎልበት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመሆኑም በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው ፥ ሚኒስቴሩም እየተከናወኑ ለሚገኙ ተግባራት ድጋፉን እንደሚያጎለብት አረጋግጠዋል።
ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በበኩላቸው ፥ ትክክለኛና የጠራ መረጃን በመያዝ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራትም ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ነው ያመላከቱት።
በክልሉ በጤናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦች እንዲመዘገብ ሚናቸውን በአግባቡ እየተወጡ የሚገኙ አካላትን ማመስገናቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!