Fana: At a Speed of Life!

በመዲናችን የመኪና ሥርቆት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣የካቲት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የመኪና ስርቆት መበራከቱን ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች ገለጹ።

እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ባለፉት 6 ወራት ብቻ 74 መኪኖች ላይ የስርቆት ወንጀል ተፈጽሟል።

በቀጣይም ችግሩን ከምንጩ ለማስቆም የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የመኪና ስርቆት ከደረሰባቸው ባለንብረቶች መካከል ወጣት መለስ ይገኝበታል፡፡ ወጣቱ በታክሲ ሥራ የሚተዳደር ባለንብረት ሲሆን ዓለም ባንክ አካባቢ እንደሚኖርና መኪናውን ከሚያሳድርበት አካባቢ የካቲት 3 ሌሊት ላይ በሌቦች ስትንቀሳቀስ በመስኮት እንደተመለከተ በር ከፍቶ ወጥቶ የድረሱልኝ ጥሪ ቢያሰማም የሚደርስለት እንዳጣና ሌቦቹ አደጋ ሊያደርሱበት እንደነበርም ገልጿል፡፡

ሌላኛው ስርቆት ያጋጠማቸው ግለሰብ ደግሞ አቶ ተመስገን ሲሆኑ፥ በተለምዶ “ዶልፊን” እየተባለ የሚጠራ ታክሲያቸው የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ባለሙያ እስኪያገኙ ወሰን አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አቁመው እንደነበረና ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኃላ ሲመለሱ ግን ማግኝት እንዳልቻሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፈሲካው ፋንታ ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ባለፉት ስድስት ወራት 74 ተሽከርካሪዎች ስርቆት ተፈጽሞባቸዋል፡፡

በመኪኖች ላይ የሚፈጸሙ የስርቆት አደጋዎችን ከምንጩ ለማድረቅ ፖሊስ ወንጀለኛውን ለመያዝ በሚያደርገው እንቅስቃሴ የኅብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ እንደሆነና ኅብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመተባበር ወንጀልን ለመቀነስ ብሎም ለማድረቅ የሚደረገውን ርብርብ እንዲያግዝ አሳስበዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.