በኬብል ስርቆት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት አልቻልኩም- የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬብል ስርቆት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት አለመቻሉን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ዛሬን ጨምሮ በያዝነው ወር ለሰባት ቀናት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት አለመቻሉን ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ መሉቀን አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
የኬብል ስርቆቱ በበርካታ ቦታዎች መፈጸሙን የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈጻሚው÷ በሰባተኛ፣ ልደታ እና ሃያት አካባቢ የተፈጸመው ዘረፋ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡም ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የሀገር ሀብት ስለሆነ ጥበቃ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የተቆረጠውን አገልግሎት ለማስጀመር የድርጅት ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑንም ነው አቶ ሙሉቀን አሰፋ የገለጹት፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!