ቻይና በድርቅ ለተጎዱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደምታደርግ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በድርቅ ለተጎዱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደምታደርግ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ገለጹ።
ሃገሪቱ በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው የአካባቢው ሀገራት አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደምታደርግ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሳኢድ ሙሳ አሊ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ ለሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ለኢትዮጵያ እና ለጅቡቲ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን÷ ይህም “በአፍሪካ ቀንድ የሰላምና የልማት ተነሳሽነት እንዲመጣ” ቻይና ለምታደርገው ተግባራዊ ድጋፍ ማሳያ ሌላው እርምጃ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።
ቻይና ከአካባቢው ሀገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነትና ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ አምባሳደር ዙ ቢንግን የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ ወደ ስራ መግባቷን ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!