ኤምባሲው በዩክሬን ለሚገኙና ከዩክሬን ወደ ፖላንድና ሌሎች አጎራባች አገሮች በመሄድ ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማግኘት የሚችሉበት ሊንክ ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬን ለሚገኙና ከዩክሬን ወደ ፖላንድና ሌሎች አጎራባች አገሮች በመሄድ ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማግኘት የሚችሉበት ሊንክ ይፋ አድርጓል፡፡
ኤምባሲው በሩስያ እና ዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምከንያት ዜጎች ወደ አጎራባች አገራት ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ከአገራቶቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች ጋር በመተባበር በተቻለ መጠን ያለችግር ማቋረጥ እንዲችሉ ሲሰራ መቆየቱን አንስቷል፡፡
አሁንም ከዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ጋር በጉዳዩ ላይ በመነጋገር ከዚህ ጋር በተያያዘው አጭር ሊንክ https://cutt.ly/qAi9vBJ በመግባት ዜጎች መረጃዎቻቸውን የት እንደሚገኙና ወደ የትኛው ድንበር ለማቋረጥ እየሄዱ እንደሆነ በማሳወቅ የዩከሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤት የኮንሱላር ጉዳዮች ክፍል ድጋፍ ማድረግ እንደሚፈልግ ያሳወቀ በመሆኑ ሊንኩን በመጠቀም ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!