Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ነገ በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት ይካሄዳል።
 
ከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት÷ በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተለያዩ ሥራወች በመከናወንላይ ቢሆኑም በህብረተሰቡ ላይ ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁሟል።
በተለይም በአሁኑ ወቅት በምግብ እህሎችና የምግብ ዘይት ላይ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱን ነው አስተዳደሩ የገለጸው፡፡
 
መንግስት ይህንን ለማረጋጋት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ ችግሩን ለመቀነስ በከተማ አስተዳደሩ ሁለት መሠረታዊ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ባደረገው አስችኳይ ስብሰባ ለሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒየን 10 ሚሊየን ብር ተዘዋዋሪ ብድር በጀት በመመድብ የግብርና ምርቶችና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተለይም በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም በበላይነህ ክንዴ ለከተማችን የሚቀርበው የፊቤላ ዘይት በወቅቱና በበቂ መጠን እየቀረበ ባለመሆኑ ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመነጋገር 883 ሺህ ሊትር ፓልም ዘይት ከውጭ ተገዝቶ በአለ በጅምላ በኩል መቅረቡ ነው የተጠቆመው፡፡
 
በነገው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት እንደሚካሄድ መገለጹን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነወ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ነዋሪዎች በተፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረጉ ያሳሰበው ከተማ አስተዳደሩ÷ ህብረተሰቡ ለሚደረገው የህግ ማስከበር ሥራ አስፈላጊውን ትብብር እዲያደርግም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.