በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 20 ሺህ ሊትር ዘይት ተያዘ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱሉልታ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 20 ሺህ ሊትር ዘይት ተያዘ፡፡
ዘይቱ በተካሄደ ድንገተኛ ፍተሻ በሕገ ወጥ መንገድ በአራት ሱቆች ተከማችቶ መገኘቱን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዘይቱ በተጨማሪ የተለያዩ ቁሳቁሶች መያዛቸውም ታውቋል።
የተያዘው ዘይትም ቀደም ሲል በነበረው ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲሸጥ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!