Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የተለያዩ ህክምና ቁሳቁስ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የተለያዩ ህክምና ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ገለጸች፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው ፥ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ኢትዮጵያ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡት የኮቪድ-19 ክትባቶች በመላው አገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲደርሱ እናደርጋለን ብሏል፡፡
በአማራ እና አፋር ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በነበረው ጦርነት የህክምና መሠረተ ልማቶች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ኤምባሲው ገልጿል።
የወደሙ እና የተዘረፉ የጤና ተቋማትን የህክምና መሳሪያዎችና መሠረተ ልማቶች ከማሟላት በተጨማሪ ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በሁለቱም ክልሎች የአልትራ ኮልድ ቼይን ማቀዝቀዣዎችን (የፋይዘር ክትባት ለማጓጓዝ እና ለማከማቸት የሚያስፈልጉ) በመግጠም ድጋፍ አድርጓል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.