Fana: At a Speed of Life!

አባትን ማጣት ያሳዝናል፤ አባት ጥላና ከለላ ነው – ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አባትን ማጣት ያሳዝናል፤ አባት ጥላና ከለላ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።
ካርዲናሉ ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት÷ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ታላቅ አባት እንደነበሩ አስታውሰው÷ አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው ሄደው ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ይጸልያሉ ብለዋል።
አክለውም አባትን ማጣት ያሳዝናል፤ አባት ጥላና ከለላ ነው ሲሉ የሀዘን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ድርቅና የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸው÷ ብጹዕነታቸው ይህን ለፈጣሪ ያሳስባሉ በማለት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለብጹዕነታቸው ነፍስም ፈጣሪ ምህረት እንዲያደርግላቸው ተመኝተዋል።
ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ የስንብት መርሃ ግብር ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.