የነጃሺ ቀን በዱባይ ኤክስፖ 2020 ማዕከል ተከበረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በምትሳተፍበት ኤክስፖ 2020 ዱባይ ማዕከል “የነጃሺ ቀን” ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተከበረ።
በመርሀ ግብሩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ÷ ኢትዮጵያ የሁሉም እምነት ተከታዮች በጋራ የሚኖሩባት አገር መሆኗን ገልጸው፥ እስልምናም ይሁን ሌሎች እምነቶች የሰው ልጆች በሰላም እና በአንድነት ተሳስበው በወንድማማችነት አብረው እንዲኖሩ የሚያስተምሩ መሆኖቸውን አስረድተዋል።
በመሆኑም የሁሉም እምነት ተከታይ አባቶችና አዋቂዎች በኢትዮጵያ ሰላምና እድገት እንዲሰፍን የእምነቶቹን ተከታዮች እንዲያስተምሩ አምባሳደር ሱለይማን ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ታሪክ ምሁር ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ለተሳታፊ እንግዶች ስለ እስልምና ሃይማኖት አስተምህሮት እና እስልምና ወደ ኢትዮጵያ የገባበትን ታሪካዊ ሂደት እንዲሁም ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ስላላት ታሪካዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ገለጻና ማብራሪያ መስጠታቸው ታውቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!