Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ለአርብቶ አደሩና ልዮ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች የ10 ዓመት እቅድ ግብዓት ማሰባሰቢያ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሄራዊ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ለአርብቶ አደሩ እና ልዮ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች የ10 ዓመት እቅድ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ አካሄደ።

ኮሚሸኑ የ10 ዓመት እቅድ ግብዓት ማሰባሰቢያው በዛሬው እለት ከባለድርሻ አካላት እና ከስድስት ክልሎች ከተወከሉ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከደቡብ፣ ከጋምቤላ፣ ከቤንሻጉልእና ከሱማሌ ክልል የተወከሉ ተገኝተዋል።

የ10 ዓመት እቅድ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይም እቅዱ የአርብቶ አደሩን ህይወት የሚለወጡ እና ምርትና ምርታማነትን የሚያሰድጉ ዘጠኝ መሰረታዊ ጉዳዮች የያዘ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

በጤና፣ ውሃ፣ መንገድ፣ በትምህርት እና በመሳሰሉት የአርብቶ አደሩን ህይወት መቀየር እንደሚቻል በውይይቱ ላይ ተነሰቷል።

የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ ዋነኛው ስላም ነው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ እና በቀበሌ መዋቅራዊ አደረጃጀት በአሰራር እና በሰዉ ሀይል ስላሙ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጻል።

የፕላን እና ልማት ኮሚሸን ምክትል ኮሚሸን ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ፥ እቅዱ ተበታትነው በመኖራቸው በልማት ተጠቃሚ ሳይሆኑ የቆዩትን አርብቶ አደር የህብርተሰብ ክፍሎች በጥናት እና

በፍቃዳቸው በመለየት በአዲስ መንደር በማሰባሰብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ያጎለብታል ብለዋል።

በአርብቶ አደሩ አካባቢ የልማት መሰፈፀሚያ ፖሊሲ ያለመኖር፣ ሰነ ምህዳሩን የጠበቀ የልማት ሰራዎች አለመስራት፣ ባለድርሻ አካላት በጋራ አለማቀድ እና አለመሰራት እንደ ችግር የተነሱ ጉዳዮቸ ናቸው።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.