Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለውጭ ሀገራት የምታቀርበውን የጥራጥሬ ምርት ለጊዜው አቆመች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለምስራቅ አውሮፓ፣ ምዕራብና መካከለኛው እስያ ሀገራት የምታቀርበውን የጥራጥሬ ምርት ለጊዜው ማቆሟን አስታውቃለች፡፡
ሞስኮ ከዩክሬን ጋር በተያያዘ የሚጣሉ ማዕቀቦች እየጨመሩ መምጣታቸውን ተከትሎ የሀገር ውስጥ የምግብ ፍጆታን ለመጠበቅ በማሰብ የጥራጥሬ ምርቶችን ለጊዜው ወደ ውጭ እንደማትልክ ገልጻለች።
በሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሚሹስቲን በተፈረመው ድንጋጌ መሠረት ሩሲያ እስከ ፈረንጆቹ ሰኔ 30 ድረስ የስንዴ፣ አጃ፣ ገብስ እና የቆሎ ምርቶችን ወደ ሀገራቱ አትልክም።
ከዚህ ባለፈም ድንጋጌው እስከ ፈረንጆቹ ነሐሴ 31 ነጭ እና ጥሬ ስኳርን ወደተለያዩ ሀገራት መላክንም ይከለክላል።
ይሁን እንጂ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶሪያ አብራምቼንኮ እንደገለፁት፥ በግለሰብ ደረጃ በተፈቀደው መጠን ልክ ምርቶቹን ወደ ውጭ መላክ አይከለክልም ነው ያሉት፡፡
በዓለም ላይ ትልቋ ስንዴ አቅራቢ ሩሲያ ከ2021 እስከ 2022 ባሉት ጊዜያት አነስተኛ ምርት መሰብሰቧን ተከትሎ የውጭ ሽያጯ አንድ ሦስተኛው መቀኑሱን አርቲ በዘገባው አመላክቷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.