Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ከመጋቢት 15 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ከመጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ አስታውቀዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ምክር ቤቱ ስለሚያደረግው መደበኛ ጉባኤ መግለጫ ሰጥተዋል።
ምክር ቤቱ ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔውን ነው የሚያካሂደው።

በጉባኤው የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም የሚገመግም ሲሆን፥ የስድሰተኛው አንደኛ መደበኛ ጉባዔን ቃለ ጉባዔን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የበጀት ዓመቱን የስድስት ወር የመልካም አሥተዳደርና የልማት እቅድ የሥራ አፈፃፀም ይገመግማልም ነው ያሉት።

ክልሉ በስድስት ወር ፈታኝ ወቅት ማሳለፉን ያስታወሱት አፈ ጉባዔዋ የፀጥታ ጉዳይና የልማት ሥራዎች በጉባዔው ሪፖርት እንደሚቀርብ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ጉባዔው የቋሚ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.