Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን በጦርነቱ ለተጎዱ የጤና ተቋማት 7 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምህረት ሜዲካል ሰፕላይ ግሩፕ እና ሲዳማ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በጦርነቱ ለተጎዱ የጤና ተቋማት የሚውል 7 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ምህረት ሜዲካል ሰፕላይ ግሩፕ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ለተጎዱ የጤና ተቋማት 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በአዲስ አበባ የምህረት ሜዲካል ሰፕላይ ግሩፕ ተወካይ ህይወት ወልዴ እንደገለጹት÷ ድርጅቱ በዋናነት መድሀኒት አቅርቦት ላይ የሚሰራ ሲሆን የተደረገው ድጋፍ የወደሙ የጤና ተቋማትን ለመገንባት ያግዛል ብለዋል፡፡

በቀጣይም በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ለመደገፍ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው ድጋፋቸው እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
በሌላ በኩል የሲዳማ ክልል 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከህክምና ቁሳቁስ በተጨማሪም የስነ ልቦና ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን የጠቀሱት የድጋፉ አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አባቢ÷ በቀጣይም ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ሀላፊ ወዘሮ ፀዳለ ሰሙንጉስ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የተደረገፍ ድጋፍ የወደሙ የጤና ተቋማትን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

በአይናለም ስለሺ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.