Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ካቢኔ ነዳጅን በህገ ወጥ መንገድ በሚያሸሹ ግለሰቦች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግሥት ሥራ አስፈፃሚ አካላት መንግሥት አሁንም ከክልሉ ከተሞች በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅን የሚያወጡና በህገወጥ ተግባር ላይ በተሰማሩ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ዕርምጃ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ውሳኔ አሳልፏል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከክልሉ ጸጥታ አመራር አካላት፣ አመራሮችና ከዞን አስተዳደሪዎች ጋር በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ሁኔታ ፣ በህገወጥ የነዳጅ ዝውውር፣ በጸጥታና በክልሉ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ከውይይቱ በኋላም ህገ ወጦች በህብረተሰቡ ላይ የፈጠሩት ዋጋ ንረትና የነዳጅ እጥረት ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም መንግስት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያወጣቸውን ውሳኔዎች መመሪያዎች እንዲሁም ህግና ደንብ የሚጥሱ አንዳንድ የነዳጅ ማደያ ባለንብረቶች መኖራቸው እንደተረጋገጠና የክልሉ መንግሥት በህገ ወጦቹ ላይ በቂ ትዕግስት ማሳየቱን ገልፀዋል።

በዚህም ህገ ወጦቹ ከድርጊታቸው ካልተቆጠቡ የንግድ ፍቃዳቸውን እስከመሰረዝ ድረስ ምህረት የሌለው ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከስምምነት ላይ መደረሱን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመጨረሻም የህግ የበላይነትን በማጠናከር ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን መታገልና ሰሞኑን በገዥው ፓርቲ አንደኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ የሶማሌ ክልል መንግሥት ካቢኔ አባላት አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.