Fana: At a Speed of Life!

የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ለአካል ጉዳተኞች ምቹና ተደራሽ የማድረግ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ለአካል ጉዳተኞች ምቹና ተደራሽ የማድረጉ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው እንዲሚገባ ተመለከተ።
ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂዷል።
የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎን ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ሚናን በዝርዝር ያካተተ ሰነድም ይፋ ተደርጓል።
የአካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማኅበራት ፌደሬሽን ተወካይ አቶ ማቱሳላ መና እንደተናገሩት÷ ከቱሪዝም ልማት ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች ቢሆኑም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ማድረግ ላይ ግን ክፍተቶች ይስተዋላሉ።
ከፍተኛ ቁጥር ያለው አካል ጉዳተኛ መኖሩን የጠቀሱት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አማካሪ አቶ ይስፋልኝ ኃብቴ÷ይህንን ያላካተተ የቱሪዝም ልማት ግቡን ሊመታ አይችልም ብለዋል።
ከቱሪዝም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሆቴሎች፣ሪዞርቶችም በአብዛኛው ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ስላልሆኑ ሊሰራበት እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቷል በመድረኩ ተሳታፊዎች፡፡
አካል ጉዳተኞች የቱሪዝም ቦታዎችን በቀላሉ እንዲጎበኙ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ቁልፍ ጉዳይ ነውም ብሏል።
አካል ጉዳተኞች ሳይቸገሩ እንዲጎበኙ ቴክኖሎጂዎቸን ጨምሮ መንገድን እና መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ላይ ሊሰራ እንደሚገባም ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
አካል ጉዳተኞችን በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት ከባለድርሻ አካላት ጋር የስምምነት ፊርማ በማድረግ ወደ ሥራ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.