ሚኒስቴሩ ከጀርመን የልማት ተቋም ጋር ያዘጋጀው የ5 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ከጀርመኑ የልማት ተቋም (ጂ አይ ዜድ)
ጋር ያዘጋጀው አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ዝግጅት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡
ጋር ያዘጋጀው አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ዝግጅት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡
የኢትዮ ጀርመን አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ዝግጅት ፕሮጀክት ዋና አላማ በሀገር አቀፍ እንዲሁም በተመረጡ ክልሎች ደረጃ አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲዎች፣ ህጎች እና ተቋማዊ አደረጃጀቶችን ለማሻሸል እንዲሁም በተመረጡ አካባቢዎች ለማሳያ የሚሆኑ የመሬት አጠቃቀም እቅዶችን በማዘጋጀት ፍትሀዊ፣ ውጤታማ እና አሳታፊ የመሬት አጠቃቀም ዕቅዶችን ለማዘጋጀት ያለመ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ስምምነቱ 5 ሚሊየን ዩሮ ሲሆን ለፕሮጀክቱ የተመደበው ገንዘብ ፈሰስ የሚደረግበት የጣምራ ፕሮጀክት የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ ይፋ አድርገውታል፡፡
በዚሁ ማብሰሪያ ዝግጅት ላይ ከተለያየ ዘርፍ ማለትም ከሲቪል ማኅበራት፣ ከልማት አጋሮች እና ከባለድርሻ አካላት የተወከሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የአስር ዓመት የልማት እቅድን ለማዘጋጀት እና ትግበራውን ለመከታተል ሥልጣን በተሰጠው የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እና የጀርመኑ የልማት ተቋም ጂ አይ ዜድ አማካኝነት ነው፡፡
በነገው እለት ደግሞ በፕሮጀክቱ የትግበራ እቅድ ላይ ከሚመለከተቻው ባለድርሻ አካላትና ቴክኒካል ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆኑበት አውደ ጥናት ይካሄዳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!