ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከዓለም ባንክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከዓለም ባንክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ታውፊላ ንያማድዛቦ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የልማት እቅዶች ዙሪያ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
በዚሁ ውይይት ላይ ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ እየተገበረች በምትገኘው የአስር ዓመቱ የልማት እቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከእነዚህ መካከል መንግስት ቅድሚያ የሚሰጣቸው የጤና፣ የመንገድ፣ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን፣ የአቅም ግንባታ እና የምግብ ዋስትና ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!