አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌና ሌሎች አመራሮች የአዌቱ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌና ሌሎች አመራሮች በጅማ ከተማ የአዌቱ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ።
ምዕራፍ አንድ የአዌቱ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ባለፈው አመት የተጠናቀቀ ስሆን ምዕራፍ 2 በከተማው ቢሺሼ የገበያ ማዕከል አካባቢ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።
ስለ ፕሮጀክቱ ገለፃ ያደረጉት የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጅብ ራያ፥ የፕሮጀክቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጠቅሰው በቀጣይ ሁለት ወራት እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ 80 ሚሊየን ብር ነው እየተገነባ ያለው።
አመራሮቹ በቀጣይ ቀናት ከህብረተሰቡ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሙክታር ጠሃ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!