Fana: At a Speed of Life!

ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሸቱ 2 ከ30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ፡፡

ሦስት የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች መነሻቸውን ብራዚል-ሳኦ ፖሎ በማድረግ በኢትዮጵያ በኩል ወደ ተለያዩ ሀገራት 1 ሺህ 895 ጥቅል ፍሬ ወይም 42 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን በቦርሳ ይዘው ለማለፍ ሲሞክሩ የኢትዮጰያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላችውን የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር አዲሱ ባለኒ ገልፀዋል፡፡

ኢንስፔክተሩ አያይዘውም ግለሰቦቹ በአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ውስጥ ግርግር በመፍጠር እና ከሰራተኞች ጋር በመጋጨት ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርጉም በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ መነሻዋን ብራዝል ሳኦ ፖሎ መዳረሻዋን ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል ዱባይ ለማድረግ 1 ሺህ 49 ጥቅል ፍሬ ወይም 21 ኪሎ ግራም ከ380 ግራም የሚመዝን ኮኬይን ይዛ የተገኘች ብራዝላዊት የኢትዮጰያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋል መቻሏን ኢንስፔክተሩ አስታውስዋል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ 15 ቀን ውስጥ 2 ሺህ 44 ጥቅል ፍሬ ወይም 63 ኪሎ ግራም ከ380 ግራም ኮኬይን መያዙን ነው የጠቆሙት፡፡

በአሁኑ ወቅት ዝውውሩን ለመከላከል በአየር መንገዱ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝና የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይም በወንጀል ምርመራ ቢሮ እየተጣራ ይገኛል መባሉን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.