Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች የተማሪ ወንበሮችን አሰራጨ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች የተማሪ ወንበሮችን ማሰራጨቱን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብዓቶች ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ ይርሳው ብርሃኔ እንደገለጹት÷ ቢሮው በ35 ሚሊየን ብር ወጭ ያሰራቸውን የተማሪ ወንበሮች በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች አሰራጭቷል፡፡
ከ12 ሺህ በላይ ወንበሮችን በማሰራት ዞኖች በጦርነቱ የደረሰባቸውን ጉዳትና የተማሪ ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ስርጭት እየተከናወነ መሆኑን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ወደ 9222 ገንዘብ በመላክ፣ በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ 9222ን በመጠቀም እንዲሁም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም ማህበረሰቡ የወደሙ ትምህርት ተቋማትን እንዲገነባ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.