Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የተጀመረው የልማት ውጥን እንዲቀጥል የዓለም ባንክ ድጋፉን ይቀጥላል- ታዎፊላ ኒያማድዛቦ

አዲስ አበባ፣ መጋት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተጀመረው የልማት ውጥን እንዲቀጥል የዓለም ባንክ ድጋፉን እንደሚቀጥል የዓለም ባንክ ቦርድ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ታዎፊላ ኒያማድዛቦ ታዎፊላ ኒያማድዛቦ ገለጹ።
ዳይሬክተሩ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ወንጂ ኩሪፍቱ በ564 ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ የለማ ስንዴን ጎብኝተዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ በኢትዮጵያ በጣም ግዙፍ የልማት ዓቅም እንዳለ መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሚከተሉት የአመራር ዘይቤና ለተደረገላቸው መስተንግዶ ምስጋና አቅርበው÷ በኢትዮጵያ የተጀመረው የልማት ውጥን እንዲቀጥል የዓለም ባንክ ድጋፉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.