በሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦድሪን በድሪ፥ ህዝባዊ መድረኩ የዜጎች ጥያቄ የሚስተጋባበት መሆኑን ገልፀዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ አያይዘውም ባለፉት ስድስት ወራት የህዝቡን ጥያቄ የሚመልሱ የተለያዩ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።
የብልፅግና ፖርቲ የህዝቦችን በጋራ የመኖር እሴትን ለማጠናከር እየሰራ የሚገኝ ፖርቲ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ሞገስ ባልቻ ናቸው።
በዚህም ፖርቲው በመስራች ጉባሄው ያሳለፋቸውን የዜጎችን የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ህዝባዊ ውይይት ማድረግ አስፈልጓል ብለዋል።
ከዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ለመፍታት ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች፣ የንግድ ስርዓትንና የሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
በመድረኩ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦድሪን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሃይማኖት መሪዎችና የፖርቲው አባላትና ደጋፊዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
በእዮናዳብ አንዱዓለም