ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ከሩሲያ ጋር እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች መቀጠላቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 14፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ከሩሲያ ጋር በተለያዩ እርከኖች እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች እንደቀጠሉ መሆናቸውን ፕሬዚዳት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ በቴሌግራም ገጻቸው በለቀቁት ቪዲዩ በሁለቱ ሀገራት እየተካሄደ ስላለው ጦርነት፣ ስለሰላም ድርድሩ ሂደት እና ጦርነቱን ተከትሎ ስለተፈጠረው መፈናቀል ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጦርነቱ በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ለሞት እና ለስደት መዳረጉን በንግግራቸው አንስተዋል።
ይህን ለማስቆምም ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ድርድር ከባድ እና አስቸጋሪ ቢሆንም ከጊዜ ወደጊዜ መሻሻል በማሳየት ወደፊት እየሄደ መሆኑንም ፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል።
ሀገራቱን ወደ ሰላም መመለስ እጅግ አስቸጋሪ እና ፈታኝ ቢሆንም የዩክሬን ተወካዮች የሰላም ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ እንደሆነ አስታውሰዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዚህም የሰላም ድርድሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥሩ መሻሻል እያሳየ ነው ብለዋል፡፡
በኪየቭ ፣በካርኪቭ ፣ዛፖሪዢያ እና ሉሃንስክ ክልሎች ውስጥ ያሉ የሰብአዊ መተላለፊያዎች በሚከፈቱበት ዙሪያም ድርድር እየተደረገ ነው ማለታቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!