የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ይጀምራል።
ጉባዔው ዛሬና ነገ የሚካሄድ ሲሆን÷ የክልሉ መንግስትን የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም እንደሚገመግም ይጠበቃል፡፡
የበጀት ዓመቱን የስድስት ወር የመልካም አሥተዳደርና የልማት እቅድ የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል፡፡
ምክር ቤቱ በመልሶ ግንባታ ላይም ውይይት ካደረገ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ እና የቋሚ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!