Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ከ490 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በቡና መሸፈኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ከ490 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በቡና መሸፈኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ የተመራ ልዑክ በጅማ ዞን ቀርሣ ወረዳ የሚገኝ የቡና ችግኝ ማፍያ ጣቢያን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ እንደተገለጸው÷ በዞኑ ከ490 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በቡና ተሸፍኗ፤ በዚህ ዓመትም 152 ሺህ ኪሎ ግራም ዘር ለተከላ ተዘጋጅቷል፡፡
በ2014/15 የምርት ዘመንም 32 ሺህ ሄክታር መሬት በአዲስ የቡና ዘር እንደሚለማና 131 ሺህ አርሶ አደሮች በሥራ እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡
አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት÷ የቡና ልማት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማሕበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ፣ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታንኳይ ጆክ፣ የጅማ ዞን አስተዳዳሪ እና የጂማ ከንቲባ ተሳትፈዋል።
በጅማ ዞን በተያዘው ዓመት 181 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
በተመስገን አለባቸው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.