የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን የአውሮፓ ህብረት አደነቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን እንደሚደግፍ ገለጸ፡፡
ህብረቱ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ÷ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ በፍጥነት ለማድረስ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ትናንት መግለፁ ይታወቃል።
መንግስት በወሰደው የግጭት አቁም ውሳኔ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በተሳለጠ ሁኔታ መድረስ እንዲችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ለሰብዓዊነት ሲባል የተላለፈው ግጭት የማቆም ውሳኔ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡም ጠይቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!