የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 30 ቶን የምግብ ነክ ቁሳቁስ እርዳታ ላከች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል ተጨማሪ 30 ቶን የምግብ ነክ ቁሳቁስ መላኳን አስታውቃለች፡፡
አገሪቱ የላከችው ተጨማሪ የምግብ እርዳታ በትግራይ ክልል የሚገኙ 5 ሺህ 700 ህጻናት እና እናቶችን ጨምሮ 7 ሺህ 100 ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አምባሳደር መሃመድ ሳሌም አል ራሺዲ÷ሀገራቸው በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል የተለያየ መጠን ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፋ ማድረጓን ገልፍ ኒውስ በዘገባው አስታውሷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!