በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ትራፊክ አደጋ ሕፃን ልጅን ጨምሮ የሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደሴ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ህጻን ልጅን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 37 ተሳፋሪዎች ቆስለው ላሊበላ ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ።
ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ከደሴ ከተማ ተነስቶ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ የነበረና ከ43 ሰው በላይ የጫነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላሊበላ ከተማን አለፍ ብሎ ሰኞ ገበያ ከምትባል አካባቢ በመገልበጡ አደጋው መድረሱን ከዋግ ኸምራ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተሽከርካሪው ተገለባብጦ ካረፈ በኋላ ቃጠሎ መነሳቱ የተገለፀ ሲሆን፥ የቃጠሎ ምክንያት ከሰው ጋር ቤንዚል መጫኑ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
በአደጋው አንድ ህጻን ልጅ ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ እስካሁን በተገኘ መረጃ 37 ተሳፋሪዎች ቆስለው በላሊበላ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ ታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!