ቻይና ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማሳለጥ ይቻል ዘንድ ግጭት ለማቆም መወሰኑን አድንቃለች።
በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷ ቤጂንግ በኢትዮጵያ ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚደረገውን አገራዊ ምክክር እንደምትደግፍ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የምታደርገውን ሰብዓዊ እርዳታ አጠናክራ እንደምትቀጥል ነው የገለጹት፡፡
መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ ግጭት ለማቆም መወሰኑን ከትናንት በስቲያ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!