Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ የባህል ሳምንት በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ባህላችን ለቱሪዝም ዕድገታችን” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የባህል ሳምንት (ፌስቲቫል) በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡

በዚህም በጠዋቱ በጎዳና ላይ ትርዒት መከበር የጀመረ ሲሆን ÷ከክልሉ በተጨማሪ የሌሎች ክልሎች የባህል ቡድን አባላት በተጋባዥነት በባህል ሳምንቱ እየተሳተፉ ነው፡፡

በባህል ሳምንቱ ላይ ሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የባህል ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በጎዳና ላይ ትርዒት፣ የባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች አውደርዕይ፣ በተለያዩ ሙዚቃ ባንዶች መካከል ውድድር ይቀርብበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፓናል ውይይት እንዲሁም የጥናትና ምርምር ሲፖዚየምም የባህል ሳምንቱ አካል እንደሚሆን ተነግሯል።

ለኦሮሞ ባህልና ኪነጥበብ ዕድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅናና ምስጋና የሚሰጥ ይሆናል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.