የውሃ ፕሮጀክቶችን የግንባታ ጊዜ መጓተት ያስቀራል የተባለ ሶፍትዌር በለፀገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውሃ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋል የዲዛይን ጥራት ችግርና የግንባታ ጊዜ መጓተት ለማስቀረት የሚያስችሉ ሶፍትዌሮች ማበልፀጉን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምሳደር አስፋው ዲንጋሞ÷ ሶፍትዌሮቹ በውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ የዲዛይን ጥራት ችግርና የጊዜ መጓተትን ለማስቀረት አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል፡፡
የመጠጥ ውሃ ፕሮጄክቶች ተደጋጋሚ የዲዛይን ማሻሻያ፣ የጥራት ጉድለትና በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቅ ለተጨማሪ ወጪና ለመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ መሆናቸውን ጠቁመው÷ የበለጸገው ሶፍትዌር የህዝቡን የመጠጥ ውሃ ፍላጎት ለማሟላትና በዘርፉ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ጭምር እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የስልጠና አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ሉሌ በበኩላቸው÷ ሶፍትዌሮች ወቅቱን ያገናዘቡ መሆናቸውን ገልጸው÷ የስራ ተቋራጮችን ለመቆጣጠር ጭምር የሚረዱ መሆናቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል፡፡
ሚኒስቴሩ በተቋሙ በበለፀጉ ሶፍትዌሮች አጠቃቀም ዙሪያ ሲሰለጥኑ የቆዩና ከሁሉም ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የውሃ ሴክተር ተቋማት የተውጣጡ 120 ባለሙያዎችን ዛሬ አስመርቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!