Fana: At a Speed of Life!

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ የግልና የመንግስት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የደብረ ብርሀን ኢንዱስትሪ ፓርክ ዝርዝር የስራ እንቅስቃሴን ማስጎብኘቱን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በ75 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባ ሲሆን÷ በ1 ሺህ 100 ካሬ መሬት ላይ ያረፈ እና 8 የማምረቻ ሼዶችን የያዘ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 በሀገሪቱ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን 30 የማድረስ እቅድ እንዳላት መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.