የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ድጋፉን በአሶሳ ከተማ ተገኝተው ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን አስረክበዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን÷ የክልሉ መንግስት ካማሺና መተከል ዞኖችን ጨምሮ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም አቅዶ አየሠራ ባለበት ወቅት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ያደረገው ድጋፍ ትልቅ አቅም ይሆናል ብለዋል።
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሰው መቋቋም ያለባቸው በእኛው በራሳችን በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!