Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሰላምና ደህንነት ጉዳዮችላይ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሁለትዮሽ አካባቢያዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ በትብብር ለመሥራ ተስማምተዋል፡፡
የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሮበርት ኪቢቹ ዛሬ በናይሮቢ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ÷ ኢትዮጵያና ኬንያ በሰላም እና ደህንነት እንዲተባበሩ የተመቻቸ ሁኔታና ዕድል መኖሩን ገልፀዋል፡፡
ጄኔራል ኪቢቹ በበኩላቸው÷ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በኬንያ ቆይታ በማድረጋቸው መደሰታቸውን ጠቅሰው÷ አገራቱ የረጅም ጊዜ ወዳጅ ናቸው፤ ይህንንም የበለጠ ማጠናከር ይገባናል ብለዋል፡፡
የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሞቹ በስልጠና፣ በሰላምና ደህንነት ማስከበር ዘርፎች ለመደጋገፍ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውንም በኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያና ኬንያ አባል የሆኑበትን የምስራቅ አፍሪካ የተጠንቀቅ ኃይልን ለማጠናከር በግንባር ቀደምትነት ለመስራት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጄኔራል ኪቢቹ መስማማታቸውም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.