Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገላሳን ያጣናቸው ይበልጥ በሚያስፈልጉን ጊዜ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአቶ ገላሳ ዲልቦ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ አቶ ገላሳን ያጣናቸው ይበልጥ በሚያስፈልጉን ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ገላሳ ዲልቦ ከተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት እና እኩልነት መታገላቸውን አውስተዋል፡፡
በተለይ በሶማሌ በነበራቸው የትግል ቆይታ ብዙ መከራ እና ችግር እንዳሳለፉ አጫውተውኝ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በቅርቡ በለውጡ አመራር በተደረገላቸው ግብዣ የሰላማዊ ትግል ጉዞ መርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ መታገል ከመጀመራቸውም ባሻገር በ2013 ምርጫ በግል ተወዳድረው የፓርላማ አባል ለመሆንም መቻላቸውንም ገልጸዋል፡፡
በትግል ውጣ ውረድ ውስጥ የገጠማቸውን በጎ እና ክፉ ለማሄስ እና ወጣቶች ከሁለቱም እንዲማሩ ለማድረግ ይተጉ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።
አቶ ገላሳ ዝምተኛ፣ አስተዋይ፣ ምክንያታዊ እና ለሰላማዊ ንግግር እጅግ የሚያመች ሰብእና የተላበሱ እንደነበሩም አንስተው÷ ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር ብለዋል።

 

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.