Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።
 
ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው የክልሉ መንግስት ያለፉ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበት እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
 
ባለፉት 6 ወራት በአስፈፃሚው አካል በተለያዩ ዘርፎች የተካሄዱ የልማት ስራዎች እና አጠቃላይ የመንግስት የስራ ዕቅድ አፈፃፀምም በዝርዝር ይቀርብበታል።
 
በክልሉ መንግስት ምስረታ ወቅት ውይይት ያካሄደበት ቃለ ጉባዔ ቀርቦ እና ውይይት ከተካሄደበት በኋላ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል ነው የተባለው።
 
የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2012 እና 2013 ዓ.ም የሴክተር መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝት ፋይናንሺያል ሪፖርት በጉባዔው እንደሚቀርብም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀን አዋጅ፣ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮን በአዲስ ለማቋቋም የተዘጋጀ አዋጅ ቀርቦ እና ሰፊ ውይይት ተካሂዶበት እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.