500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የሰበአዊ ድጋፍ ትግራይ ክልል ደርሷል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክልል መድረሱን የአለም ምግብ ድርጅት ገለጸ።
ወደ ክልሉ በየብስ የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ እንቅስቀሴ መጀመሩን ተከትሎ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።
በዛሬው ዕለትም 500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ በድረጅቱና አጋር አካላቶች አማካኝነት ወደ ክልሉ መድረሱን ነው ያስታወቀው።
እርዳታውን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰላም እንዲያልፉ የአፋር ክልል ላደረገው ትብብርም ድርጅቱ ምስጋናውን አቅርቧል።
ድርጅቱ በሰሜናዊ አፋር በዳሎል፣ በራኽሌ እና ኮኔባ አካባቢዎች ለሚገኙ ሰዎች የሚሰራጭ 1 ሺህ ሜትሪከ ቶን የምግብ እህል እርዳታ ከሰሞኑ አካባቢው ላይ እንደሚደርስም ነው የገለጸው።
መንግስት በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ድጋፍ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል የግጭት ማቆም ውሳኔ ማድረጉና በየብስ የሚደረገው ድጋፍም እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወቃል።