ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በሃምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው የተጻፈውን “የተካደው ሰሜን ዕዝ ” የተሰኘ መጽሃፍ መረቁ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሃምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው የተጻፈው “የተካደው ሰሜን ዕዝ” የተሰኘ መጽሃፍን በዛሬው ዕለት መርቀዋል።
በሃምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው የተጻፈው “የተካደው ሰሜን ዕዝ” የተሰኘው መጽሃፍ በዛሬው ዕለት በብሄራዊ ቴአትር ተመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምር ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለጸሃፊው ሃምሳ አለቃ ጋሻዬ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መጽሃፉ አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ክህደት እና ቡድኑን ለመደምሰስ ከህልውና ዘመቻው ጀምሮ እስከ ህብረ ብሄራዊ ዘመቻ የተከናወኑ የዘመቻ ስራዎችን የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
በመላኩ ገድፍ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!