ቻይና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን ገልጸዋል።
አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን በአማራ፣ ሲዳማ እና ደብቡ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ የኢንዱስትሪ መንደሮችን መጋቢት ወር ላይ መጎብኝታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጉብኝታቸውም አምባሳደሩ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሁለቱም አገራት ሰፊ የሥራ ዕድል እና ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን በመፍጠር ጉልህ ሚና የሚጫወት እንደሆነ መረዳታቸው ነው የተገለጸው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!